Ethiopianism

ሎጅክ (አመክንዮ) እና መቀሌ (መስቀሉ አየለ)

መስቀሉ አየለ

በወታደራዊ ሹመቱ ከዘጠና ስምንት በመቶ በላይ ጀነራል የምትሾሙት ከትግራይ ነው። ደህንነቱም እንዲሁ ቁልፍ በሚባለው ቦታ ወደ መቶ ፐርሰንት የሚጠጋው ቅጥረኛ ሁሉ አሁንም ከትግራይ ነው።  


በዚህም የተነሳ የመከላከያም ሆነ የደህንነት መስሪያ ቤቱ የስራ ቋንቋ ትግረኝ እስከመሆን ደርሷል ማለት ይቻላል። ይሔንን አይን ያወጣ ዘረኝነት ምን ብለን እንረዳው ተብለው በተጠየቁ ቁጥር መልሳቸው አንድና አንድ ነበር።

"ብዙ የትግራይ ተዎላጅ ተሿሚወች ያሉን የመሳሪያ ትግሉ በትግራይ ስለጀመረና ደርግን በመጣሉ ረገድ ትልቁን ድርሻ የተጫወቱት የትግራይ ልጆች ስለነበሩ በአገልግሎት ብዛት ሹመት ሲመጣ ከነሱ የተሻለ የአገልግሎት ዘመን ያለው ስለማይኖር ነው" የሚል ሰንካላ መልስ ሲሰጡ ኖረዋል። ሽፈራው ሽጉጤም ባቅሙ ይህችኑ አረፍተነገር ቃል በቃል አጥንቶ ሳይከልስ ሳይሰልስ መናገሩን አስታውሳለሁ።

ዛሬ ይህ ስርዓት እስከ አጥንቱ ነቅዟልና አቃቢ ህግ ማሰሩን ከማን ይጀምር ሲባል "ትግሬን ለይታችሁ ልታጠቁ: ይላሉ። ከእ ዲህ አይነት የ አይምሮ ዘገምተኝነት ይሰውራችሁ።

ነፍሱን አይማረውና ኢህአዴግ የተባለ ቅምቡርስ በህይወት ሳለ አራት ድርጅቶችን አቅፎ ነበር። ለምሳሌ ብአዴን ከአማራ ውጭ የሆኑ ሰዎች የተሰገሰጉበትን ያህል ህወሃት ደግሞ አንድም ትግሬ ያልሆነ አባል አልነበረውም።ስለዚህ ሲጀመር ህወሃት ዘረኛ ድርጅት ነው ማለት ነው።

ይህን ሁኔታ በጣም ቀላል በሆነ ማቲማቲካል ሎጅክ( አመክንዮ) ስናየው፤

  • ሕወሃት ሁሉ ትግሬ ነው።
  • ሕወሃት ሁሉ በመላ አገሪቱ ከልመና እስከ ላይኛው የስልጣን ከፍታ እንበለ ይሉኝታ ሁሉንም በሚባል ደረጃ አሰፍስፎ ይዟል። የዚህ ዘመቻ አንዱ አካል አገሪቱን መርዞ የያዛትን የዘረፋ ሰንሰለት መበጣጠስ ነው። ስለዚህ ዘራፊዎች በሙሉ ሊታደኑ ይገባቸዋል፤
  • ዘራፊዎቹ ባለስልጣኖቹ ናቸው፤

  • ባለስልጣኖቹ ህወሃቶች ናቸው፤
ስለዚህ በዚህ ሎጅካል አርጉዪመንት የእስር ዘመቻው በዋናነት ትግሬዎች ላይ ማነጣጠሩ አመክንዮዋዊ ነው። በመሆኑም፤ ህወሃት አንድም ዘረኛ አንድም ሰፍሳፋ ባይሆን እና ስልጣኑን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ አጋርቶ ቢሆን ኖሮ እስሩንም ይጋሩለት ነበር።

ሲደመደም፤
ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል።

No comments