Ethiopianism

ለመንግስት የተጻፈ ደብዳቤ…… እና ሌሎች

ለመንግስት የተጻፈ ደብዳቤ…… እና ሌሎች


ለመንግስት የተጻፈ ደብዳቤ…… እና ሌሎች

የባንዲራው ብሄር

(ምንጭ ፌስቡክ)
ትልቁን ማንነት እውነት የሚፍቁ
በባንዲራው አምላክ እስኪ ይጠየቁ
ባ'ረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ባንዲራ ላይ
የትኛው ብሄር ነው ተፅፎ የሚታይ?

የጠላሁሽ ለታ

(ልዑል ሀይሌ)


የጠላሁሽ ለታ....
ዓለም ትዙርብኝ
ፀሐይም አትውጣ ጨለማው ይምጣብኝ
ጨረቃዋም ትጥፋ ከዋክብት ይርገፉ
ውቅያኖሶች ደርቀው ዕፅዋቶችም ይጥፉ

"የምፃተኛው ኑዛዜ"
(በእውቀቱ ስዩም)

ካ’ገር ጫፍ እስከጫፍ በጥላህ ከልለህ
ተራራው የኔ ነው ለምን ትለኛለህ?
እንኳንስ መሬቱ አንተም ያ’ንተ አይደለህ።
ወንዙ ድርሻዬ ነው ለምን ትለኛለህ?

አልወድህም እንጂ
(ከፌስቡክ የተገኘ)

አልወድህም እንጂ
ባለፈው እንዳልኩህ
አልወድህም እንጂ እኔ ከወደድኩህ
እኔ ያንተ እያለሁ አተ የኔ እያለህ
ሲኦል ነው መድረሻው አፈቀርኩህ ያለህ

ለመንግስት የተፃፈ ደብዳቤ
(በላይ በቀለ ወያ)

እንደምነህ መንግስት? ፣ እኔ አለሁ በደህና
ባመቻቸህልኝ የልማት ጎዳና
ለወንበር ስጋፋ ፣ ኪሴን ተዘርፌ
ታክሲ ለመጠበቅ ፣ ሰልፍ ተሰልፌ
አለሁልኝ በተድላ
በቀን ሶስት ጊዜ...
ቁርስ ምሳ ራቴን ፣ መከራ ስበላ

ሳልነግርሽ…
(በላይ በቀለ ወያ)

አፍቅሬ እንዳጣሁሽ…
በነብያቶች አፍ፣
ፍልስፍና ሚመስል ፣ ትንቢት ተነገረ
ታምር የሚሰራ…
ጎትቶ ጎትቶ ፣
ግመሉ ሲሻገር ፣ መርፌው ተሰበረ፡፡
በመርፌ ቀዳዳ ፣ ግመል አሻገረ
በሰባራ መርፌ….
ክር ሆነሽ እያጠርሽ ፣ ኖራለሁ ስለፋ፡፡
ፍቅርሽን ከፍቅሬ ፣ ባንድነት ልሰፋ
ይኸው እደክማለሁ…
አይደለም ምኞቴ
(በዕውቀቱ ስዩም)

አይደለም ምኞቴ
ለምለም አንገትሽ ላይ : ክንዶቼን መጠምጠም
ዳሌሽ ላይ መንሳፈፍ: ጭንሽ ማሃል መስጠም
እይደለም ምኞቴ

የተካደ ትውልድ
(በዕውቀቱ ስዩም)

የተካደ ትውልድ
አይዞህ ባይ የሌለው
ታዳጊ የሌለው
ወይ ጠባቂ መላክ፤ ወይ አበጀ በለው
ደርሶ ከቀንበሩ የማይገላግለው

No comments