Ethiopianism

ራያ በለቅሶ ሲቃ ተከባለች ህዝቡ መሄጃ አጥቷል



ራያ በለቅሶ ሲቃ ተከባለች ህዝቡ መሄጃ አጥቷል

የራያ ህዝብ በግፍ ሲጨፈጨፍ ቆሞ ማየት የለም የጌታቸው አሰፋ ሚኒሻ ሰራዊት በራያ ተጣቂዎች አሩን እየበላ ነው፡፡ በአሀኑ ሰዐት ነገሮች መልካቸውን ለውጠዉ ህዝቡም አምሯል፡፡ ነዋሪዉ እራሱን ወደመከላከል ተሻግሯል አላማጣ ከተማ እብሪተኛውን ጦር ዞሮበል በማለት የራያ ሚሊሻ መሳሪያውን አዞሮ ገጥሟል!!! ግፋ የራያ ሚሊሻ!!!

ህወሃት መቃብሩን በደንብ አርቆ እየቆፈረ ነዉ፡፡ መቃብሩም ራያ ላይ ይሆናል፡፡ የራያ ህዝብ እንኳን ልጆቹን በወሮ በላ ታጣቂ ተነጥቆ እንዲሁም የሚተኛ ህዝብ አይደለም፡፡ ለራያ ወጣት አንድ መልክት አለኝ፡፡ ህወሃት በደም የሰከረ እድሜ ልኩን የሰዉ ነብስ ሲያጠፋ ኖሮ ከመላ ኢትዮጵያ ፈርጥጦ መቀሌ የተጠራቀመ ግኡዝ አካል ነዉ፡፡  


ህወሃት የፈሩት ከመሰለዉ ደም ከማፍሰስ ወደኋላ አይልም፡፡ ህወሃትን እንደ እባብ አናት አናቱ ሲቀጠቀጥ ብቻ ነዉ የሚገባዉ፡፡ የአማራ እና የኦሮሞ ወጣት እንደ እባብ ቀጥቅጦ ነዉ ያባረረዉ፡፡ በአንድ ወቅት በመቶ ሺህ ሰራዊት ታጅቦ ጎንደር የደረሰዉ ህወሃት በአንድ ኮሎኔል ብትንትኑ እንደወጣ ስነግራችሁ የዛሬ መቶ አመት ታሪክ ሳይሆን የዛሬ ሶስት አመት ታሪክ ነዉ፡፡ 

አንድ ጀግና ኮሎነል የበተነዉ እና ከኮሎኔሉ ምላጭ የተረፈዉ እና እግሬ አዉጭኝ ብሎ የፈረጠጠዉ ነዉ ዛሬራያ ላይ የሚረብሽ፡፡ ለጀግናዉ ራያ ደግሞ ይሄን ትርፍራፊ ጉንዳን መጨፍለቅ አያቅተዉም፡፡  

ተደራጅቶ ከእናቱ ጉያ እስኪገባ ማጣደፍ ያስፈልጋል፡፡ የወንድሞቻችን ደም እንዲሁ በከንቱ ፈሶ አይቀርም፡፡ የአማራ ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ከራያ ህዝብ ጋር ይቆማል ለነጻነቱም ይታገላል፡፡ Miky Amhara 

በአላማጣ ከተማ የሚካሄደው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሏል። የመከላከያ ሰራዊት አባለት ወደ ስፍራው ቢገቡም፣ የልዩ ሃይሉ አባላት የሚፈጸሙትን ጥቃት ማስቆም እንዳልቻሉ ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ዛሬም እንደ ትናንቱ በርካታ ሰዎች በልዩ ሃይል አባላት እየተደበደቡ ነው። የጭስ ቦንቦችም እየተተኮሱ ነው። በከተማው ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ESAT

ራያ አላማጣ ራርሄ ከተባለ ቦታ አሁን ብቻ ሶስት ወገኖቻችን በአልሞ ተኳሽ የህወሓት ወታደሮች ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። Amanuel Abinet

አላማጣ ከተማ የትግራይ ክልል ልዩ ጦር እና የራያ ሚሊሻ የተኩስ ልውውጥ በማድረግ ላይ ናቸው።
የፌደራል መንግስት እና የመከላኪያ ሃይል በአካባቢው እልቂት ከመከስቱ በፊት ወደ ቦታው ሊደርስ ይግባል።

አሁን በዚህ ሰዓት በሁለት ኦራል መኪና የመከላከያ ሰራዊት አላማጣ ገብቷል። ሆኖም ግን በሚያሳፍር መልኩ መከላከያው ወጣቶች ላይ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡

በመከላከያ ሰራዊቱ አሁን ሁለት ወጣቶች ተመትዋል። በዚህ ሳቢያም ህዝቡ ከፍተኛ እሮሮ እያሰማ ይገኛል ራያ በለቅሶ ሲቃ ተከባለች ህዝቡ ከዛም ከዚህ መሄጃ አጥቷል።
ፍትህ ለራያ ህዝብ



No comments