Ethiopianism

የኔስ ሔዋን ~ ክፍል - 5 [ከአስጌ]

የኔስ ሔዋን ~ ክፍል - 5 [ከአስጌ]

ብዙወች ጨርቃቼውን ጥለው አብደዋል። ግራ ተጋብተዋል። ጎዳና ወጥተዋል። ከአላማቼው ተሰናክለው በጫት በሲጋራ በሱስ ተጠምደዋል።


ሰለዚህ ሜሮን ይህንን ነገር ባታስቢው ነበር እሚሻለው። ነገር ግን ሳታስቢው በደራስ ኖሮ ባስቆምኩሽ ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር። ግን አሁንም እኔን የመርሳትና ሌላ ላንች የሚመጥን ላንች የሚገባ በጣም በርካታ ሰው ስላለ ወደ ሌሎች ሰዎች እንድትመለከች ነው እምነግርሽ። ማስታወስ ያለብሽ ግን የትምህርት ቤት ፍቅር እስከየት ነው እሚሄደው ?
የሚለውን ጥያቄ በደንብ አስቢበትና መልሱን ለራስሽ ንገሪው።


እና እንብኝ እያልካት ነው ማለት ነው አለች መልሱን እንደሆነ ለማረጋገጥ የፈለገችው በታሪክ መስማት የተጠመደችው ተሳፋርይዋ ጓደኛየ።


አወ አልኩና ቀጥየም ልንገርሽ ሜሮን ግን ከዚህ በውሀላ እኔጋ በምንም አይነት ነገር እንዳትደርሽብኝ ስለስጦታሽና ስላደረግሽልኝ ነገር በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ። ግን እኮ ሜሮን ስለ እ ምን ልትላት ነው አለች አድማጯ ተሳፋሪ።
አስጨርሽኛ አልኩና ግን እኮ ሜሮን አንችጋ እውነተኛ ፍቅር መኖሩን እርግጠኛ መሆን አለብሽ። 


በጊዜያዊ ስሜትና በአይን ፍቅር እንዳይሆን የተታለልሽው። እውነተኛ ፍቅር ከሆነ ግን አዝናለሁ ምንም ልረዳሽ አልችልም። እኔ በዚህ ሰአት ስለ ፍቅር ምናምን እሚባል ነገር ማሰብም ማስታወስም አልፈልግም አልችልምም።
ቻው ቻው ቻው
ናትናኤል

ደብዳቤውንም ፅፌ እንደጨረስኩ ስሜንና ፊትማየን እንደልጅቱ አድርጌ አስቀምጨ እሮብን ለማየት አመሻሹን የማታ የፀሀይ ጨረር ለመሰናበት እንደተለመደው በጣም የምወደውን የእግር ጉዞ ለማድረግ የብርድ መከላከያ ይሆናሉ ብየ ያሰብኳቼውን ጃኬት ሱሪና ጫማ ለብሼ ስልኬን ይዤ እንደተለመደው እያዳመጥኩና እያዋዘው ወደ አዲስ አበባ የሚወስደውን መንገድ ይዤ የአንድ ሙዚቃ ከስልኬ ከፍቼ መራመድ ጀመርኩ።  

በነገራችን ላይ የድሮ ሙዚቃ በጣም ነው እምወድ። ከምርህ ነው አለች ይህች የታሪክ ተመራማሪ እምትመስል ታሪክ ሰሚዋ የባስ ጓደኛየ። አወ በእግሬ እስከ 1፡30 ድረስ ወክ ማድርግ ስለምወድ እማዳምጠውም የድሮ ሙዚቃ ነው። 

እሽ ከዛስ። ከዛማ የዛን ቀን ግን የመጀመርያ ሙዚቃ ሳደምጥ በጣም ገረመኝ። ሙዚቃውን አሁንም ድረስ ስለምወደው አደምጠዋለሁ። ምን ነበር እሚል አለች ይህችው ጓደኛየ። ፀሀዬ ነው ልጋብዝሽ
"ብቸኝነቴን እኔ እማስታውሰው
አልጀመርኩም ነበር ፍቅር ከሌላ ሰው

ሙዚቃውን አንቺም እንደምትወጅው ተስፋ አደርጋለሁ። ለነገሩ ይመስለኛል የድሮ ሙዚቃ የሚያደምጥ ትውልድ ላይ ያለን አይመስለኝም። ግን ብቻ ይሄን ሙዚቃ እወደዋለሁ እስከ በቅርብ ጊዜ አደምጠው ነበር።  


ታድያልሽ የ7ኛ ክፍል ትምህርት አመት በዚህች ልጅ የተነሳ ህይወቴ ምስቅልቅል አለች። የትምህርት ቤቱ ተማሪዋችም የሚያወሩት አጣን የናንተን ስም ብቻ ነው ማትፋት የምንፈልገው ያሉ ይመስል ወሬያቼው ሁሉ ሰለኛ ብቻ ሆነ። ታድያ አንድ ቀን ወሬው ከትምህርት ቤትሸልፎ ከቤተሰቦቼ ጀሮ አንኳኩቶ ገባ...........

ክፍል 6 ይቀጥላል

No comments