Ethiopianism

የኔስ ሔዋን ~ ክፍል - 3 [ከአስጌ]

የኔስ ሔዋን ~ ክፍል - 3

እንደገባው ቀጥታ ያንን ደብተር አወጣውት። የመጀመርያ እይታየም ከደብተሬ ውስጥ በሚያብለጨልጭ ነገር የታሸገ ስጦታ አየሁ። ያተገውን ነገር መፈታታት ስጀምር አንድ መፅሀፍ መሳይ ነገር በወረቀት ተጠቅልሎ ተመለከትኩኝ። ወረቀቱ ላይም ፅሁፍ ነበረው።

ምን እሚል ነበር አለች ታሪክ ሰሚዋ ጓደኛየ። ፅሁፉም "ውስጡን ከማየትህ በፊት በጀርባ ያለውን ወረቀት አንሳና አንብበው ይላል። ከዛ ያንን የታሸገ ነገር ሳልፈታ ገልበጥ ሳደርገው በፕላስተር የተያዘ ወረቀት አየሁ። 

የተላጠቀውን ወረቀትም አስለቅቄ ፈታታውትና ላነብ ተዘጋጀው በነገራችን ላይ ከፈለግሽ ላነብልሽ እችላለሁ አሁንም ድረስ ወረቀቱ አለኝ። በናትህ አንብብልኝ አለች የተፃፈውን ለመስማትና ለማወቅ እየተዘጋጀች። እኔም ወረቀቱን ከዋሌት ፖርሳየ አውጥቼ ማንበብ ጀመርኩላት።

በቀይ እስኪብሪቶ የፃፈውን አሳየዋትና ሌላውን እኔው ላነብላት ተዘጋጀው። በቀይ መስመር የተፃፈውም ምን ይላል መሰላችሁ 

[አበባ ይዣለሁ በትንሿ እጣቴ
ፍቅርህ አቃጠለኝ በወጣትነቴ]

ከታችም ያለውን እንዲህ አድርጎ ማንበቤን ተያያዝኩት። ይቅርታ ናቲዬ ደህንነትህን ሳልጠይቅህ እንዴት ነህ የኔ ቆንጆ። ይህን ወረቀት ስፅፍልህ ላንተ ካለኝ አመለካከት ጋ ያለኝን ስሜት ልገልፅልህ ፈልጌ ነው።  

ግን አንተን በዚህች ወረቀት ብገልፅህ አንተን ከማማትና ከማንቋሼሽ በምንም አይተናነስም። ይልና መሀል ላይ አነስ ያለች ልብ ቅርፅ ብጦር ተወግታ እሚያሳይ ምስል አስቀምጣለች ከልብ ቅርፁ ቀጥሎ ያለው ፅሁፍ ደግሞ እንዲህ ነበር እሚለው። እሽ ቀጥል እየሰማውህ ነው አለች አድማጯ በጉጉት። 

እኔም ቀጠልኩና ...ፍቅር ፀጋ ነው ከተባለ ታዲያ ለኔ ለምን መከራና ስቃይ እንዲሁም ፈተና ሆነብኝ። ግን ግን እኮ እጠይቅሀለሁ እያልኩ ፍቅር ማለት ምን ማለት ነው ? ማለቴ ባንተ አመለካከት በኔ ግን ልንገርህ ፍቅር ማለት መውደድን ሳይጠብቁ ዝም ብሎ መውደድ ነው።  

ለምን ግን ከኔ ፍቅር ያዘሽ እንዳትለኝ ምክንያቱን አልነግርህም። ለማንኛውም መናገርም መፃፍም ብዙ ችሎታ የለኝም። ማለት ስላንተ ወይም አንተን ለመግለፅ መሞከር ከላይ ስለገለፅኩልህ መደጋገም ነው እሚሆንብኝ እናም አንድ ንገር እንድትተባበረኝ እፈልጋለሁ።

ስማ እኔ አንተን ማፍቀሮን ማንም እንዲሰማ ስለማልፈልግ ለማንም ይህን ወረቀት እንዳታሳይ እንዳታወራምም። ስማ ደግሞ መልሱን ላስብበት እንዳትለኝ እሽ ስትለኝ ወድያውኑ የእንትና ዘፈን ትዝ አላለኝም መሰለሽ ስል እድማጯ ቀበል አደረገችና የማን ስትለኝ ያች ላስብበት እንዳትለኝ አሁን እያለች እምትዘፍነዋ ልጅ ሰላት ፈገግ አለችና እሽ ከዛስ አለች። 

ከዛም ቀጠልኩና ማንበቤን ተያያዝኩት ላስብበት እንዳትለኝ ዝምታ እንደ እሽታ ነው እሚቆጠረው። እሁድ ጠዋት ቤተክርስቲያን በር ስትመጣ እንገናኝ ይላል።
አፍቃሪህ ሜሮን
I love you


በመጨረሻም የፊርማ ማረጋገጫ እፈልጋለሁ ያልኳት የመስል ልዩ ፊርማዋ ነው መሰለኝ አስቀምጣበታለች። ወረቀቱን አንብቤ እንደጨረስኩ ወደ ታሸገው ነገር ተመልሼ መፈታታት ጀመርኩ።

ኧረ በስማም ሲገርም ምን ቢሆን ጥሩ ነው ገምች? እስዋም ለመገመት መፅሀፍ እንደሆነ ካረጋገጠች በውሀላ ፍቅር እስከ መቃብር አለች አይደለም ስል እሽ ብቻ ስለ ፍቅር እሚያወራ መፅሀፍ አለች እሱም አይደለም አልኩና መፅሀፉ ፍቅር እስከ መቃብር እንዳይመስልሽ ሌላችነው ደግሞ ሌላ ነው ስትባይ ስለ ፍቅር የሚያወራ መፅሀፍ እርእስ ለመፈለግ እንዳትደክሚ መፅሀፉ.. ......

ክፍል 4 ይቀጥላል

No comments