Ethiopianism

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከቪኦኤ ኃላፊዎች ጋር ተገናኙ



ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከቪኦኤ ኃላፊዎች ጋር ተገናኙ

የአሜሪካ ድምፅ ለባለሞያዎቹ ሥልጠና ሲሰጥ ያገር ውስጥ ጋዜጠኞችንም ቢያካትት ፍላጎታቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታውቀዋል።
የአሜሪካ ድምፅ ለባለሞያዎቹ ሥልጠና ሲሰጥ ያገር ውስጥ ጋዜጠኞችንም ቢያካትት ፍላጎታቸው መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአሜሪካ ድምፅ የአፍሪካ ዲቪዥን ዳይሬክተር ንጉሤ መንገሻንና የአፍሪካ ቀንድ ማኔጂንግ ኤዲተር ትዝታ በላቸውን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

የአሜሪካ ድምፅ በኢትዮጵያና በጎረቤት ሃገሮች ለሚገኙ ዘጋቢዎቹ እስካለፈው ዓርብ የቆየ የአንድ ሣምንት ሥልጠና አዲስ አበባ ላይ ሰጥቷል።
በኢሕአዴግ መንግሥትና በአሜሪካ ድምፅ መካከል ላለፉት 27 ዓመታት ከዘለቀ ውጣ ውረድ ያልተለየው ግንኙነት በኋላ አንድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የጣቢያውን ኃላፊዎች ተቀብሎ ሲያነጋግር ይህ የመጀመሪያው ነው።

ለተጨማሪ መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።


No comments