Ethiopianism

የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በይፋ ገንዘብ መሰብሰብ ጀመረ

የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ

(ኤፍ ቢ ሲ) የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በይፋ ገንዘብ መሰብሰብ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የዳያስፖራ ትረስት ፈንዱ ከዛሬ ጀምሮ በይፋ ገንዘብ መሰብሰብ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ከሁለት ወራት በፊት መከፈቱ ይታወሳል።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከወራት በፊት በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸው እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

በወቅቱ በውጭ ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በየቀኑ ቢያንስ አንድ ዶላር ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ለተለያዩ የልማት ስራዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀው ነበር።

በዚህም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ተሳትፎ ለማቀናጀትና የልገሳውን ገንዘብ ለማሰባሰብ፥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በሚል ስም ሂሳብ መከፈቱም የሚታወስ ነው።

የሂሳብ ቁጥሩም 1000255726725 ሲሆን፥ በዛሬው እለትም በይፋ ገንዘብ መሰብሰብ ጀምሯል።

ገንዘቡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ስዊፍት አድራሻ እና CBETETAA በመጠቀምና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዓለም አቀፍ ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን በመጠቀም የሚገባ ይሆናል።

ገንዘብ አስተላላፊዎቹ ዌስተርን ዩኒየን፣ ኤክስፕረስ መኒ፣ ቦሌ አትላንቲክ ኢንተርናሽናል፣ መኒ ግራም፣ ዳሃብሽል መኒ ትራንስፈር፣ አል አንሳሪ (ካሽ ኤክስፕረስ)፣ ወርልድ ሬሚት፣ ትራንስፋስት መኒ፣ ካህ ኤክስፕረስ መኒ ትራንስፈር፣ ጎልደን መኒ ትራንስፈር፤

ላሪ ኤክስቸንጅ፣ ተወከል መኒ፣ ዜንጅ ኤክስቸንጅ፣ ፓኮ መኒ፣ ኢርማን ኤክስፕረስ፣ ባካል መኒ ትራንስፈር፣ ዲቫይን (ብሉ ናይል)፣ ዳዊት መኒ ትራንስፈር፣ ቲ እና ዋይ ሬሚት እንዲሁም አስጎሪ መኒ ኤክስፕረስን መጠቀም ይቻላል።

No comments