Ethiopianism

ገና የምጥ መጀመሪያ ነው!! (መስቀሉ አየለ)

ገና የምጥ መጀመሪያ ነው

የቀን ጅቡ አንድ ብሎ ኢትዮጵያን መግዛት ሲጀምር ሁሉንም ነገር በዘር ፖለቲካ አሰመረው። የቀን ጅቡ ይህን የጅል ቀመር ያዋጣኛል ብሎ የጀመረው የራሴ መሰረት የሚለው ህዝብ ከመላ ኢትዮጵያ ህዝብ አንጻር አምስት በመቶ ገደማ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ ነው።  


ይህ በደናቁርት የሚመራ ቡድን ከላይ የተቀመጠውን ቀመር የተማረው አያቶቹ አሽከር ከሆኑለት ሰላቶ ጣሊያን መሆኑ ነው።

ችግሩ ከዘጠና ሚሊዮን በላይ የሆነውን ቀሪ ህዝብ "በራሴ አምሳል በፈጠርኳቸው ሎሌዎች አማካኝነት እድሜ ልክ መግዛት እችላለሁ" ብሎ መንገድ መጀመሩ ነበር።አባዱላን አዲስ ለገሰን አይነት አይነት ተውሳኮች ልብ ይሏል።  


ነገር ግን ይኽ ቡድን ትናንት የኢትዮጵያ ጉዳይ ብቸኛ ዘዋሪ ከነበሩት መንግስቱ ሃይለማርያምና ጥቂት አጋሮቹ ጋር ውጊያ ብሎ ላይ ታች ብሎ ይሆናል። 

ያን ግዜ ቀሪው ህዝብ ባገሩም ሆነ በማንነቱ ጉዳይ ባይተዋር ነበረና በመሃል የተፈጠረው ክፍተትና የደርግ እንደስርዓት ከቀዝቃዛው ጦርነት ጋር አብሮ ማክተም እንዲሁም የሻቢያ እርዳታ ይህን አስካሪስ ወደ ስልጣን እንዳመጣው መካድ አይቻልም።

ዛሬ ግን ሌላ ቀን ነው።  

  1. ልዩነቱ ከፖለቲካ በላይ አልፎ የማንነት ጉዳይ፣ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ሆኖት አረፏል።
  2. ይህ ደግሞ ፖለቲካውን በጣም ቀላል እና ሁሉንም አስታፊ እንዲሆን ሲያደርገው በዚህ ዘመን በቀን ጅቡና በቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ስላለው ችግር ለመረዳትም ሆነ ለማስረዳት በአንድ የየትኖራ ገበሬና በፕሮፌሰር ጥላሁን ይልማ መካከል ምንም አይነት የግንዛቤ ልዩነት የለም ማለት ይቻላል።< /li>
ይኽ በመሆኑ ደግሞ ፖለቲካውን በጣም ቀላል አድርጎታል ብቻ ሳይሆን ዛሬ በድፍን ኢትዮጵያ ህጻን ሽማግሌ፣ ትንሽ ትልቅ፣ የተማረ ያልተማረ፣ ሴት ወንድ፣ ጎንደር አርባ ምንጭ ሳይል ሁሉም እስከ ጥፍሩ እንዲነከርበት አበክሯል።

ሆነ ተብሎ ለሩብ ክፍለዘመን የዘር ፖለቲካን የመንግስት ፖሊሲ አድርገው ካለመኖር ወደመኖር ያመጡት እኒህ ከዘራቸው በላይ ማሰብ የማይችሉ የሃሳብ ድውያን የጥረታቸውና የክፋታቸው ፍሬ የሚያጣጥሙበት የመጨረሻው ሰዓት ላይ መድረሳቸውን ልባቸው አውቆታል። 

ያም ሆኖ ግን የሁሉ ነገር ተንታኝ የሁሉ ነገር አድራጊና ፈጣሪ ነን ሲሉ የኖሩት ከስብሃት ነጋ እስከ አባይ ጸሃየ ምላሳቸው ከትናጋቸው ተጣብቆ ቃላት ብቻ ሳይሆን አየር ጭምር አጥሯቸው ድራሻቸው እንደጠፋ ግልጽ ሆኗል።

የማይቀረው ፍልሚያ ሲጀመር ደግሞ ትንቅንቁ እንደ ትናንቱ ከጥቂት የደርግ ማሽነሪዎች ጋር አይደለምና ውጤቱን ሳይታለም የተፈታ ያደርገዋል።

ስለዚህ ዛሬ ቀመሩ ዘር በመሆኑ በመሪና በተመሪ መካከል ልዩነት ሳይኖር መቶ ሚሊዮን ህዝብ ዳር እስከዳር ተጠራቶ በሁሉም አቅጣጫ ነጋሪት በሚጎስምበት ሁኔታ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ተይዞ ወደ "ኳስ ሜዳ" ለመውረድ መድፈሩ የሚያዋጣ ስሌት ከሆነ እናያለን። 

የዚህን ውስብስብ ጣጣ ሙሉ ስእል ለማየት ደግሞ አካይስቶቹ ባይሞቱ አያረጁም። አሁን እየታየ ያለው ግን ገና የምጥ መጀመሪያ ነው።

No comments