Ethiopianism

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ለዘንድሮው የቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ አጀንዳ ድጋፋቸውን ሰጡ

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2011 (ኤፍቢሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአርጀንቲና ቦነስ አይረስ ለሚካሄደው የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ የድጋፍ መልዕክት አስተላልፉ።

ስብሰባው ወደ ፊት በሚጠበቁ ስራዎች፣ በመሰረተ ልማት፣ ፆታዊ ጉዳዮች እና በምግብ ዋስትና ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ለሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ማውሪሲዖ ማክሪ ባስተላለፉት መልዕክት፥ መሪዎቹ ዓለም ለተጋረጠባት ችግሮች መፍትሄ በሚሆኑ ሀሳቦችና ሁሉን አቀፍ እድገት ማምጣት በሚቻለበት ሁኔታ ላይ እንዲወያዩ ነው መልዕክት ያስተላለፉት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትክከለኛና ፍትሃዊነት የሰፈነበት ማህበረሰብ ለመፍጠር እና ዓለም አቀፍ ሰላምና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የወጣቱን እምቅ ኃይል ለመጠቀም መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የአፍሪካ የወደፊት ብርሁ ተስፋ ከአህጉሩ የዘለለ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አፍሪካ አለም አቀፍዊ ትብብሯን ለማጠናከር ጥራትና ስፋት ያለው ስራ መስራት ይጠበቅባታል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ዘለቂ የሆነ ኢንቨስትመንትን በመሳብ በ2025 የአፍሪካ የኢንዱስቲሪ ማዕከል ለመሆንና መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ የያዘችውን ግብ ተግባራዊ ለማደረግ ተወዳዳሪነቷን እንደምታሳድግ ነው የገለፁት።

በአሁን ወቅት የግሉ ባለሀብት በኢንዱስትሪ ዘርፍ የጎላ ተሳትፎ እንዲኖረው እና ለወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል በተሻለ ሁኔታ ለመፍጠር ለዓለም ገበያ በሚቀርቡ ምርቶች ላይ ትኩረት መደረጉን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ የመንግስት ተቋማት ወደ ግል የማዘዋወርና ኢኮኖሚውን ገበያ ላይ የተመሰረተ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ነው በመልዕክታቸው የገለፁት።

የግሉን ዘርፍ የተሻለ ለማድረግ ፋይናንስ የሚደረግበት አዲስ አሰራር ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንም ነው ያነሱት።

በኤፍሬም ምትኩ

No comments