Ethiopianism

"ስለ ህዝበ ውሳኔም ስለ መገንጠልም የተነሳ ነገር የለም! የሶማሌ ክልል ተ/ፕ/ት ሙስጠፋ ኦማር



የሶማሌ ክልል ተ/ፕ/ት ሙስጠፋ ኦማር

የዶ/ር አብይን መንግስት ወይም የፓለቲካ አቅጣጫ ማጥላላት ወይም መቃወም እንድ ነገር ነው! የበሬ ወለደ አይነት ተረትተረት በመፍጠር ግን መሆን የለበትም!  


አስመራ ላይ በተደረገው ስምምነት መሰረት ኦብነግ እንደ ሌሎች ትጥቅ ይዞ ስንቀሳቀሱ የነበሩት ተቃዋሚዎች የትጥቅ ትግሉን አቁሞ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ አገር ውስጥ ገብቶ ለማካሄድ ነው የተስማማው! ስለ ህዝበ ውሳኔም ስለ መገንጠልም የተነሳ ነገር የለም!

ለማንኛውም ግን በምስራቅ በኩል የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የሚጠበቀው በሶማሌ ዝህብ ፍቃድና ፍላጎት እንጂ በሌሎች ጩኸት አይደለም!

ትናንት ናይሮቢ ውስጥ ኦሮሞ አገር እያመሰ ስለሆነ በቃ አንቀፅ 39 ጥቀሱና ተገንጥለናል በሉ ብለው አብዲ ኢሌይን ሲያበረታቱ የነበሩት ኮንትራባንድስቶች ናቸው ዛሬ ዶ/ር አብይን ሶማሌ ሊያስገነጥል ነው ብለው የሚወቅሱት!

ከኮንትራባንድስቶች ጭፍጨፋ የተረፋው የሶማሌ ህዝብ ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ ጋር በሰላም ለመኖር የሚፋልግ ህዝብ ስለሆነ የሰሜን ሰዎች የፓለቲካ ቁማር መጫወቻ ባያደርጉት ጥሩ ነው!

No comments