Ethiopianism

ይሄ የራያ የመጨረሻው ትልቁ ሞት ነው! (ያሲን ሞሃመድ)


መግደል ፍትህንና የበላይነትን ያመጣል የሚሉ አካላት ከመግደላቸው እንጂ ከሚገድሉት ፍጥረት ጉዳይ የላቸውም!!

ትህነግ ትውልድ ጨራሽ፣ ሰው ጤፉ፣ ስልጣን ህልውናው ነው የምንለው በምክንያት ነው። በባህር ዳርና በወልዲያ እናቶችንና ህጻናትን በግዴለሽነት ተኩሶ የጨፈጨፈው የትህነግ ጀሌ እነሆ ትናንት ራያ አላማጣ ላይ ይህችን እንቡጥ ቀጥፏል።

ትህነግ የቆሰለ ጅብ ነው። ትህነግ ሰው በላ አውሬ ነው። ስልጣኑን ለማራዘም በመንገዱ ሁሉ ያገኘውን የሚማማግድና የሚያቃጥል ራስ ወዳድ፣ጨካኝና አረመኔ ስብስብ ነው። በዛ ሁሉ ደም ያልተጸጸቱ ገዳዮች ቆመው ሊያስቡ ከቶ አይችሉም።

የዮሃንስ ልጆች ለራያ የሚራራ አንጄት፣ የሚያስብ ህሊና ከቶ ሊኖራቸው አይችልም። ማንነታችንን አጥፍተዋል፣ መሬታችንን ወረዋል። የእነሱ መግደል አይደንቅም፣ ይልቁን የእኛ ጉዳሞቹ አለን ማለት ይገርማል። እኛ ራሳችንን በፌስቡክ ዋሻ ወሽቀን ህጻናትንና ታዳጊዎችን የምንማግድ ጉዳሞች ነን።

ራያ ክብሩና ሞገሱ የተናደው እኛ ራያን በተረከብንበት በዚህ ዘመን ነው። እነዛ ወንዶች ድፍን አበሻ ለአጼው ሲሰግድ ሞት ይሻላል ሲሉ በወንድነት የሞቱ የጀግንነት ፈርጦች ናቸው!!  

እኛ በህጻናት የግፍ ደም ለመንጻት ከህወሃትና ኢህአዴግ ፍትህን የምንለምን ግሞች ነን። ግም ትውልድ፣ ግም ወንድ በሴት ልጁና በእናቱ ደም ሊፈወስ ወደ ሰማይ ያንጋጥጣል። አዎ፣ ራያ በታሪኩ በህወሃት ጅሪዎችና ምንደኛ "ሙህራኑ" የተናቀውን፣ የተንቋሸሸውን ያክል መቼም ተዋርዶና ሞቶ አያውቅም!!  

ይሄ የመጨረሻው ሁሉ መጨረሻ ነው!! እናቶች በእንቦቅቅላ ሕጻናት ልጆቻቸው ሞት አስፋልት ላይ ዋይ ሲሉ ፌስቡክ ላይ ተለጥፎ የእናቱን የሙሾ ፎቶና ቪዲዮ የሚያይን ወንድ ልጅ ሆኖ ከመፈጠር የማነስን ያክል ማነስ የለም!!
ራያ ጀግና ነው ይሉትን ዘፈንህን ከዚህች ቀን በኋላ አትዘፍናትም፥ አልዘፍናትም። ሽታየዋ ምጥቻሽ ያድርገኝ!!
ምን ማለት ይቻላል? ምንም።

No comments