Ethiopianism

የዘር-ማፅዳት ወንጀል በአሰላ አንዣቧል - ከንቲባውም ጆሮ ዳባ ልበስ ብለዋል (ግርማ ካሳ)

የዘር-ማፅዳት ወንጀል በአሰላ አንዣቧል

አሰላ ከተማ የተዋበች ከተማ ናት። ሕብረ ብሄራዊ ከተማ ናት። በአጼ ሃይለስላሴ ጊዜ የአሩሲ ፣ በደርግ ጊዜ ደግሞ የአርሲ ዋና ከተማ ነበረች። የአንድ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ። እንደ መቀሌ፣ እንደ አዋሳ።

ሆኖም ግን አሰላ በኢሕአዴግ ዘመን ከወዳደቁ ከተሞች መካከል አንዷ ናት። በርካታ በከተማዋ ይኖሩ የነበሩ ኦሮሞ ያልሆኑ የሌሎች ማህበረሰባት አባላት፣ በዘር ፖለቲካው ምክንያት ከተማውን ለቀው ሄደዋል። አንድ የማወቃቸው በአሰላ ብዙ ቢዝነስ የነበራቸው ጉራጌዎች፣ ይሄ የኦሮሞነት ፖለቲካ ሳቸጋሪ ስለሆነባቸው፣ ቢዝነሳቸው ይዘው አዋሳ ገብተዋል።

እንደዚያም ሆኖ አሁን በአሰላ ቁጥሩ ቀላል የማይባል ኦሮሞ ያልሆነ ማህበረሰብ አለ። እንደውም አሁን በከተማዋ አብዛኛው ነዋሪ ኦሮሞ ያልሆነው እንደሆነ ነው የሚነገረው። ሆኖም ግን እነዚህ ዜጎች በአገራቸው፣ በከተማቸው መጤ ናችሁ በመባል፣ የማስፈራራትና የዛቻ ዘመቻ ተጀምሮባቸዋል።  


የከተማ ነዋሪዎች ለከተማው አስተዳደር አቤቱታ ቢያቀርቡ ምንም ምላሽ ማግኘት አልቻሉም። ህዝቡ በአገሩ እየተዛበት እስከመቼ እንደሚኖር ግልጽ አይደለም።የሚያሳዝነ ደግሞ ሕዝብን ይጠብቃሉ የተባሉት የኦሮሞ ክልል ባለስልጣናት እንደውም ከበስተጀርባ ይሄንን አይነት ክፋት የሚያበረታቱ መሆናቸው ነው።

ኢትዮጵያዊያን በቡራዪ እንደሆነው፣ ከሆነ በኋላ፣ የሐዘን መግለጫ መስጥት ምን ዋጋ አለው። የኦሮሞ ፖሊስና ሃላፊዎች የሌላውን ማህበረሰባት ደህንነት መጠበቅ አይችሉም። አይቻሉም ብቻ ሳይሆን ይፈልጋሉ ብሎ ለማመንም አስቸጋሪ ነው። አብዛኛው ኦህዴድ ውስጥ የተጠራቀመው የቀበሌ፣ የወረዳና የዞን አመራሮች የጅዋር አድናቂዎችና ተከታዮች፣ ኦነጋዊ የጥላቻ አስተሳሰብ ያላቸው ናቸው። እነዚህ የሕዝቡን ደህንነት መጠበቅ በጭራሽ አይቻሉም።

በመሆኑም በአስችኳይ በአርሲ ዞን የፌዼራል ፖሊስና መከላከያ ገበቶ ፣ ሕግና ስርዓት እንዲያስጠበቅ እማጸናለሁ። የቡራዩ እልቂት እንዲሁ የመጣ አይደለም። የቡሯዩ መንፈስ በቅርቡ በሻሸመኔና በባሌ/ጎባ የነበረው፣ ከሃያ አመታት በፊት ደግሞ በአርባ ጉጉና በበደኖ የነበረው የዘረኝኘትና የጥላቻ መንፈስ ነው። ምንጩ አንድ ነው። ከመጠን ያለፈ፣ ኦሮሞን በመጥቀም ላይ ሳይሆን፣ ሌላውን ማህበረሰብ በመጥላት ላይ የተመሰረተ የኦሮሞ ፖለቲካ ጽንፈኝነት።

በአገር ቤት ያላችሁ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እንደ ኢሳት ያሉ የሜዲያው አባላት ወደ አሰላና አካባቢዋ በመሄድ ጉዳዩ አገራዊ ትኩረት እንዲሰጠው እንዲያደረጉም በአክብሮት እጠይቃለሁ።

ጦማሪ ስንታየሁ ቸኮል በአሰላ ያለውን ሁኔያ እንደሚከተለው አስፍሯል፡
በአሰላ ከተማ የጅምላ አፈሳ የእስር ዘመቻዉ እንደቀጠለ ነው፡፡ በቅርቡ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ አሰላ ከተማ ላይ ስጋት እንዳጃበበ መናገራቸውና የችግሩ ፈጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ መግለፃቸው ይታወቃል።

ይሁን እንጅ በአሁኑ ሰዐት ነገሮች አስከፊ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡ ከወደ አሰላ የሚመጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ ለረጅም ጊዜ ተዋልደውና ቤተሰብ መስርተው በሚኖሩ የሌላ ብሄር ተወላጆች ላይ ጥቃት በማድረስ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ በሚሉ ኃይሎች፣ ከፍተኛ ጭንቀት በሰዎች ዘንድ ፈጥሯል።

በተለይ የአሰላ ከተማ ከንቲባ በሰጡት አሉታዊ ንግግር ምክንያት የተበሳጩት ነዋሪዎች ከ20 ሺህ ሰዉ በላይ በአደባባይ ኮሚቴ ሰይሞ ለጥያቄዎቹ መልስ በመጠበቅ ቢቆይም ኮሚቴዎችን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች በግፍ ከቤታቸው እየተጎተቱ በመታሰር ላይ እንደሚገኙ የአሰላ ነዋሪዎች ይገልፃሉ፡፡

እሳካሁን በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ዝርዝር እንደደረሰን እናሳውቃለን፡፡

No comments