Ethiopianism

እስካሁን 10,000 ዜጎች ተፈናቅለዋል፤ ጥበቃ አሁንም የለም (ሜስ ደሞዝ)

እስካሁን 10,000 ዜጎች ተፈናቅለዋል

የአካባቢው ሰውም ስጋት ላይ ነው። ሀገር የምትረጋጋው ግድያን ጭካኔን በማውገዝ አይደለም። እንደ መሪ ስርአት የሌላቸው ነገሮችን እርምጃ ወስደህ ስትቀጣ ነው።

የክልሉ መሪ ላይ ተስፋ ቆርጫለሁ። የነበረኝም ተስፋ ኢምንት ነበር። የክልሉ ፓሊስ ለጥ ያለውን የቡራዩን መንገድ መልካምድር አስቸግሮን ቶሎ አልደረስንም ሲል ንቀት ነግሮናል። አሁንም ጥበቃ የለም። ኢቨን ተፈናቃዮቹ ያሉበት ቦታ ጥበቃ የለም።

አብዩ አንተ ላይ ያለኝ ተስፋ ጨርሶ አላለቅም። ህዝብ አይኑ አንተ ላይ ነው።

አሁን ላይ እየተፈጠረ ያለውን የአውሬነት ተግባር አስቁመህ ኢትዮጵያን ወደ ሰላሟ ካልመለስካት ሌላው ስራህ ጥቅም የለውም። ኤርትራን አሰብን የመን ድረስ የኢትዮጵያ ግዛት ብታረግ we will not consider it as benefit. ተለቃቅመው ገደል ይግቡ።

መጀመሪያ የመሪ ያለህ እያለ የሚጮኸውን አንተን አምኖ እያለቀሰ ያለውን ህዝብን ምረጥና ኢትዮጵያዊ ሁንና እምባውን አብስለት። ደህንነቱን መልስለት።  


ማስተዛዘን ፍቅር መስበክ ለግዜው ይብቃህ። Take action! ለዛ ደሞ ሁሉም ከጎንህ ነው። ሰኔ 16 ሊደግፍህ የወጣው ህዝብ ሀገርህን ታደግ ዝመት ብትለው አብሮህ ጉድጓድ የሚገባ ነው። አይቶ አይቶ ከተወህ ደሞ መቼም መልሰህ የማታገኘው ወገንህ ነው።

No comments