Ethiopianism

Ethiopian Music : Dan Admasu (4 kilo) አራት ኪሎ - አዲስ ዜማ ዳን አድማሱ (ከግጥም ጋር)

Dan Admasu (4 kilo)


Ethiopian Music Dan Admasu (4 kilo) 

ዳን አድማሱ (4 ኪሎ) 
New Ethiopian Music 2018(Official Video)   





ናስማስርሽ መውዜር ዝናር
ፍቅር አልገዛ ዲናር
ኩራትሽን ቀን አስጥሎ
አየን አራት ኪሎ

ወርቅ አልማዝሽ ሞልቶ ቢናር 
ፍቅር አልገዛ ዲናር
ኩራትሽን ቀን አስጥሎ
አየን አራት ኪሎ

አራት ኪሎ 
አራት ኪሎ 
ፊት በር አራዳ ዳኛው ከላይ 
ክሴን ሰማኝ ቶሎ ቶሎ ቶሎ

አራት ኪሎ 
አራት ኪሎ
 
ድምፄን ሰማኝ ቶሎ ቶሎ ቶሎ

አብደላ ካኒው ልብስ ሹመት ቀሚስሽ
ምን ነበር ሰው መውደድ ባይከለክልሽ
ነግሰሽ ካለፍቅር ሁሉም ከሚል አቤት
ተወደሽ በቀረ መባል ቀዳማዊት 
ባትበድያት ትናንት አንዲት ደሃ ነፍሴን
ስም ይቆይሽ ነበር እንደ ጥሩ ሐማሴን

ዳሩ ማንን ሰምተሽ ሳለሽ ክንደ ብርቱ
አርገሽው ጩኸቴን ወይ እሪ በከንቱ
የፓርላማው ሰዓት ባይዞርም ደቂቃው
ቀን ሲቆጥር ክሶኝ ጊዜ ሆነን ዳኛው 

እናንዬ እናንዬ
እናንዬ እናንዬ

እኔ የአርበኛ ልጅ ነኝ 
እናንዬ
ጆሊ ባር ጊርጊሮ
እናንዬ
ፈርቶ አይሞት አራዳ 
እናንዬ
በማተቡ ኖሮ 
እናንዬ
በአለወልድ አልነሳኝ 
እናንዬ
ስለቴን በከንቱ
እናንዬ
የተገፋን ሰሚ 
እናንዬ
ባሓታ አለች እናቱ 
እናንዬ
እናንዬ እናንዬ
እናንዬ እናንዬ

ሲሄድ ባራምባራስ ሲመለሱ ራስ
ወትሮም ደንቆን ነበር ያንቺ አነጋገስ
በሰገነትሽ ላይ ሰቅለሽ ገበርባሬ
ጥበብ ነው ብትይው የደነቀ ወሬ
ደጅሽ ቢከለከል የእልፍኝሽ አዳራሽ
መሆኔ ላልቀረ ያንቺን አልጋ ወራሽ 

እናንዬ እናንዬ
እናንዬ
ናስማስርሽ 
መውዜር ዝናርሽ
ፍቅር አልገዛ 
ወርቁ ዲናርሽ
ኪዳን ገድል 
ባሓታም አልተማርሽ
የካኽኑን 
ደውል አልሰማሽ 

ወርቅ አልማዝሽ ሞልቶ ቢናር 
ፍቅር አልገዛ ዲናር
ኩራትሽን ቀን አስጥሎ
አየን አራት ኪሎ

አራት ኪሎ 
አራት ኪሎ 
ፊት በር አራዳ ዳኛው ከላይ 
ክሴን ሰማኝ ቶሎ ቶሎ ቶሎ

አራት ኪሎ
 
አራት ኪሎ 
ድምፄን ሰማኝ ቶሎ ቶሎ ቶሎ

ለፍቅር አዋቂ ካላነሰ ወዶ
ምን ያደርጋል ፊደል የአቁፋዳ ባዶ
የአውራ ዶሮ ቁንጮ ስሙ ነው ኮከን
ስንቱ ቆቡን ጫነ ያልተማረውን 
አልበጀሽ ሰላሳው ያተረፍሽው ዲናር
ባብይ ጦም ያዢና ነፍስሽ ፍቅርን ይማር
 

በቄስ ሰፈር ካህን እንዳናስገዝትሽ
ለካስ መቼ ጠፋ አበምኔት ቤትሽ
ከአቡን በላይ ነው እያልሽ ክብሬና ማዕረጌ
ፊትም አልተመለስሽ በአምስት ኪሎ እጨጌ

እናንዬ እናንዬ
እናንዬ እናንዬ

ሽማግሌም ልከን
እናንዬ 
መልሰሻል ከበር "ፌርማቶሪ! "
እናንዬ
ነውር የሌለው ቤትሽ 
እናንዬ 
ትልቅ አይከበር
እናንዬ
መቀመጫ ጠፍቶ 
እናንዬ 
ሰው ሁሉ ሲቸገር
እናንዬ
ለማን አርገሽው ነው
 
እናንዬ 
ያንን ሁሉ ወንበር
እናንዬ
እናንዬ እናንዬ
እናንዬ እናንዬ

ሊቀ መኳስሽን ወደውት ያጩት
ነገር አዋቂ ነው ዳኛ ነው ሲሉት
በተማረው ድጓ በፃፈው ግንዘት
ድረስ ድረስ አሉት ግባተመሬት 
የአካፋው ሚካኤል ያለው ስድስት ኪሎ
ዘመን አሳየኛ አንቺን ከእጄ ጥሎ

እናንዬ እናንዬ
እናንዬ

ናስማስርሽ 
መውዜር ዝናርሽ
ፍቅር አልገዛ 
ወርቁ ዲናርሽ
ኪዳን ገድል 
ባሓታም አልተማርሽ
የካኽኑን 
ደውል አልሰማሽ 

እኔም አልፈልግ አንቺም ሄደሻል
ሁሉም አበቃ ተለያይተናል
እንዲኽ ሊያሳየኝ ቀን አንቺን ጥሎ
ስንቱን አለፍነው ወይ አራት ኪሎ
ወይ አራት ኪሎ
ወይ አራት ኪሎ
ወይ አራት ኪሎ
ወይ አራት ኪሎ

ዜማና ግጥም
ዳን አድማሱ

No comments