ልዩ ጥንቅር - በአቶ በረከት ስምዖን አስተያየት ላይ ብአዴን የሰጠው ምላሽ
አቶ በረከት የመንቀሳቀስ መብታቸውን የገደበው የመንግስት አካል ይሁን ሌላ በግልጽ ያስቀመጡት ነገር የለም። የብአዴን የአሁኑን አመራር ክፉኛ የወቀሱት አቶ በረከት ስምዖን የተበላሹ አመራሮች ናቸው ሲሉም ኮንነዋቸዋል።
የቀድሞ የብአዴን ከፍተኛ አመራርና የኢህአዴግ ቁልፍ ሰው አቶ በረከት ስምዖን የመንቀሳቀስ መብቴ ተገድቧል ሲሉ ገለጹ።
ታዲያስ አዲስ ከተሰኘ የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ አሁን ባለው ሁኔታ በሀገሪቱ የተለያዩ ቦታዎች ለመንቀሳቀስ ገደብ ተጥሎብኛል ብለዋል።
አሁን በመሪነት የተቀመጡት የብአዴን ሰዎች ወደ አደገኛ አቅጣጫ እያመሩ በመሆኑ ህዝቡ ሊያስቆማቸው ይገባል በማለት ገልጸዋል።
No comments